ኢዮብ 7:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ተጋድሎ አይደለምን?ዘመኑስ እንደ ምንደኛ ዘመን አይደለምን?

2. የምሽትን ጥላ እንደሚመኝ አገልጋይ፣ደመወዙንም እንደሚናፍቅ ምንደኛ፣

3. እንዲሁ ከንቱ ወራት ታደሉኝ፣የጒስቍልና ሌሊቶችም ተወሰኑልኝ።

4. በተኛሁ ጊዜ ‘መቼ ነግቶ እነሣለሁ?’እላለሁ፤ ሌሊቱ ይረዝማል፤ እስኪነጋም እገላበጣለሁ።

ኢዮብ 7