ኢዩኤል 1:18-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. መንጎች እንደ ምን ጮኹ፣ከብቶቹ ተደናግጠዋል፤መሰማሪያ የላቸውምና፤የበግ መንጎች እንኳ ተቸግረዋል።

19. አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ያልተነካውን መሰማሪያ እሳት በልቶታልና፤የዱሩን ዛፍ ሁሉ፣ ነበልባል አቃጥሎታል።

20. የዱር አራዊት እንኳ ወደ አንተ አለኸለኹ፤ወራጁ ውሃ ደርቆአል፤ያልተነካውንም መሰማሪያ፣ እሳት በልቶታል።

ኢዩኤል 1