ኢሳይያስ 62:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጽድቋ እንደ ማለዳ ወጋገን እስኪፈነጥቅ፣ድነቷ እንደሚያንጸባርቅ ፋና እስኪታይ፣ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም።

2. መንግሥታት ጽድቅሽን፣ነገሥታት ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔር አፍ በሚያወጣልሽ፣በአዲስ ስም ትጠሪያለሽ።

3. በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል፣በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።

ኢሳይያስ 62