ኢሳይያስ 55:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።

12. በደስታ ትወጣላችሁ፤በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ተራሮችና ኰረብቶች፣በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣ያጨበጭባሉ።

13. በእሾኽ ፈንታ የጥድ ዛፍ፣በኵርንችት ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል።ይህም የእግዚአብሔር መታሰቢያ፣ሊጠፋ የማይችል፣የዘላለም ምልክት ይሆናል።”

ኢሳይያስ 55