ኢሳይያስ 54:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “አንቺ መካን ሴት፤አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፤ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ባል ካላት ሴት ይልቅ፣የፈቷ ልጆች ይበዛሉና”ይላል እግዚአብሔር።

2. “የድንኳንሽን ቦታ አስፊ፤የድንኳንሽን መጋረጃዎች በትልቁ ዘርጊ፤ፈጽሞ አትቈጥቢ፤ገመዶችሽን አርዝሚአቸው፤ካስማዎችሽንም ቀብቅቢ።

3. ወደ ቀኝም ወደ ግራም ትስፋፊያለሽ፤ዘሮችሽ መንግሥታትን ይወርሳሉ፤በባድማ ከተሞቻቸውም ይኖራሉና።

ኢሳይያስ 54