ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ገና ድሮ ነገርሁህ፤ከመፈጸማቸው በፊት አስታወቅሁህ፤ ይህም፣‘ጣዖቶቼ ይህን አደረጉ፤ከዕንጨት የተቀረጸው ምስልና ከብረት የተሠራው አምላኬ ይህን ወስኖአል’እንዳትል ነው።