ኢሳይያስ 45:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ጒልበት ሁሉ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤አንደበትም ሁሉ በእኔ ይምላል፤ብዬ በራሴ ምያለሁ፤የማይታጠፍ ቃል፣ከአፌ በጽድቅ ወጥቶአል።

24. ስለ እኔም ሲናገሩ፣ ‘ጽድቅና ኀይል፣ በእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ይላሉ።”በእርሱ ላይ በቍጣ የተነሡ ሁሉ፣ወደ እርሱ መጥተው ያፍራሉ።

25. ነገር ግን የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ሞገስንም ያገኛሉ።

ኢሳይያስ 45