ኢሳይያስ 45:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ‘በፊትህ እሄዳለሁ፤ተራሮችን እደለድላለሁ፤የናስ በሮችን እሰብራለሁ፤የብረት መወርወሪያዎችንም እቈርጣለሁ።

3. በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ፣እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቅ ዘንድ፣በተሰወረ ስፍራ የተከማቸውን ሀብት፣በጨለማም ያለውን ንብረት እሰጥሃለሁ።

4. ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ስለ መረጥሁት ስለ እስራኤል፣አንተ ባታውቀኝ እንኳ፣በስምህ ጠርቼሃለሁ፤የክብርም ስም ሰጥቼሃለሁ።

5. እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም፤ከእኔ በቀር አምላክ የለም።አንተ ባታውቀኝም እንኳ፣እኔ አበረታሃለሁ።

ኢሳይያስ 45