ጠራቢ በገመድ ይለካል፤በጠመኔ ንድፍ ያወጣል፤በመሮ ይቀርጸዋል፤በጸርከል ምልክት ያደርግበታል።በሰው አምሳል ይቀርጸዋል፤የሰውንም ውበት ያለብሰዋል፤በማምለኪያም ስፍራ ያስቀምጠዋል።