ብረት ቀጥቃጭ መሥሪያን ይይዛል፤በከሰል ፍም ላይ ይሠራዋል፤ጣዖትን በመዶሻ ቅርጽ ይሰጠዋል፤በክንዱም ኀይል ያበጀዋል።ከዚያም ይራባል፤ ጒልበት ያጣል፤ውሃ ይጠማል፤ ይደክማል።