ኢሳይያስ 4:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚያን ቀን ሰባት ሴቶችአንዱን ወንድ ይዘው፣“የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፣ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።

2. በዚያን ቀን የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ ያማረና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን ኵራትና ክብር ይሆናል።

3. በጽዮን የቀሩት፣ በኢየሩሳሌምም የተረፉት፣ በኢየሩሳሌም በሕይወት ከተመዘገቡት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።

ኢሳይያስ 4