ኢሳይያስ 33:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፣መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ።

4. ሕዝቦች ሆይ፤ አንበጣ እንደሚሰበስብ ብዝበዛችሁም ይሰበሰባል፤ሰዎችም እንደ ኩብኩባ ይጨፍሩበታል።

5. እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ጽዮንን በጽድቅና በፍትሕ ይሞላታል።

6. እርሱ ለዘመንህ የሚያስተማምን መሠረት፣የድነት፣ የዕውቀትና የጥበብ መዝገብ ይሆናል፤ እግዚአብሔርንም መፍራት የዚህ ሀብት ቍልፍ ነው።

ኢሳይያስ 33