ኢሳይያስ 19:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ግብፅ የተነገረ ንግር፤እነሆ፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ላይ ተቀምጦወደ ግብፅ ይመጣል፤የግብፅ ጣዖቶች በፊቱ ይርዳሉ፤የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።

2. “ግብፃዊውን በግብፃዊው ላይ አስነሣለሁ፤ወንድም ወንድሙን፣ባልንጀራ ባልንጀራውን፣ከተማም ከተማን፣መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።

3. የግብፃውያን ልብ ይሰለባል፤ዕቅዳቸውንም መና አስቀራለሁ፤እነርሱም ጣዖታትንና የሙታንን መናፍስት፤መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ምክር ይጠይቃሉ።

ኢሳይያስ 19