ኢሳይያስ 12:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤“እግዚአብሔር ሆይ፤ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤ደግሞም አጽናንተኸኛልና እወድስሃለሁ።

2. እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ ነው፤እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ድነቴም ሆኖአል።”

3. ከድነቴ ምንጮችውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።

ኢሳይያስ 12