1. ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ እነሆ፤ የጎመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት ነበረ።
2. እርሱም፣ “አሞጽ ሆይ፤ ምን ታያለህ?” አለኝ። እኔም፣ “የጎመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልሁ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፍጻሜ መጥቶአል፤ ከእንግዲህም አልምራቸውም።”
3. ጌታ እግዚአብሔር፣ “በዚያ ቀን የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ወደ ዋይታ ይለወጣል፤ እጅግ ብዙ የሆነ የሰው ሬሳ ወድቆ ይገኛል፤ ዝምታም ይሰፍናል” ይላል።
4. እናንት ችግረኞችን የምትረግጡ፣የምድሪቱንም ድኾች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤
5. እንዲህም ትላላችሁ፤“መስፈሪያውን በማሳነስ፣ዋጋውን ከፍ በማድረግ፣በሐሰተኛ ሚዛን በማጭበርበር፣እህል እንድንሸጥ፣የወር መባቻ መቼ ያበቃል?ስንዴም ለገበያ እንድናቀርብ፣ሰንበት መቼ ያልፋል?”
6. ድኻውን በብር፣ችግረኛውንም በጥንድ ጫማ እንገዛለን፤ግርዱን እንኳ በስንዴ ዋጋ እንሸጣለን።”