ሰቆቃወ 1:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ፣እንዴት የተተወች ሆና ቀረች!በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው፣እርሷ እንዴት እንደ መበለት ሆነች!በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፣አሁን ባሪያ ሆናለች።

2. በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤እንባዋ በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል፤ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል፣የሚያጽናናት ማንም የለም፤ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ጠላቶቿም ሆነዋል።

ሰቆቃወ 1