ማሕልየ መሓልይ 4:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ጎሕ ከመቅደዱ በፊት፣ጥላውም ሳይሸሽ፣ወደ ከርቤ ተራራ፣ወደ ዕጣኑም ኰረብታ እወጣለሁ።

7. ውዴ ሆይ፤ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤እንከንም አይወጣልሽም።

8. ሙሽራዬ ሆይ፤ ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤አዎን ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤ከአንበሶች ዋሻ፣ከነብሮች ተራራ፣ከኤርሞን ራስ፣ ከሳኔር ጫፍ፣ከአማና ዐናት ውረጂ።

9. እኅቴ ሙሽራዬ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል፤በአንድ አፍታ እይታሽ፣ከሐብልሽም በአንዱ ዕንቊ፣ልቤን ሰርቀሽዋል።

10. እኅቴ ሙሽራዬ፣ ፍቅርሽ እንዴት ደስ ያሰኛል!ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛየሚያረካ ነው፤የሽቱሽም መዐዛ ከቅመም ሁሉ ይልቅ የቱን ያህል ይበልጥ!

11. ሙሽራዬ ሆይ፤ ከንፈሮችሽ የማር ወለላ ያንጠባጥባሉ፤ከአንደበትሽም ወተትና ማርይፈልቃል፤የልብስሽም መዐዛ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው።

ማሕልየ መሓልይ 4