2. ጥርሶችሽ ወዲያው ተሸልተው፣ከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።
3. ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤አፍሽም ውብ ነው፤ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጒንጮችሽ፣ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።
4. ዐንገትሽ አምሮ የተሠራውን፣በላዩም የጦረኞች ጋሻዎች ሁሉ ያሉበትን፣ሺህ ጋሻዎች የተንጠለጠሉበትን፣የዳዊትን የመጠበቂያ ማማ ይመስላል።
5. ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ ሆነው የተወለዱ፣በውብ አበቦች መካከልም የተሰማሩ፣ሁለት የሚዳቋ ግልገሎችን ይመስላሉ።
6. ጎሕ ከመቅደዱ በፊት፣ጥላውም ሳይሸሽ፣ወደ ከርቤ ተራራ፣ወደ ዕጣኑም ኰረብታ እወጣለሁ።
7. ውዴ ሆይ፤ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤እንከንም አይወጣልሽም።
8. ሙሽራዬ ሆይ፤ ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤አዎን ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤ከአንበሶች ዋሻ፣ከነብሮች ተራራ፣ከኤርሞን ራስ፣ ከሳኔር ጫፍ፣ከአማና ዐናት ውረጂ።