ማሕልየ መሓልይ 1:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር።

2. በከንፈሩ መሳም ይሳመኝፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛልና።

3. የሽቱህ መዐዛ ደስ ያሰኛል፤ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነው፤ታዲያ ቈነጃጅት ቢወዱህ ምን ያስደንቃል

4. ይዘኸኝ ሂድ፤ እንፍጠን፤ንጉሡ ወደ ዕልፍኞቹ አምጥቶኛል።በአንተ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፤ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እንወድሳለን።አንተን እንደዚህ ማፍቀራቸው ትክክል ነው።

5. እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤እኔ ጥቊር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ጥቊረቴ እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎችም ነው።

ማሕልየ መሓልይ 1