ሚክያስ 3:11-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. መሪዎቿ በጒቦ ይፈርዳሉ፤ካህናቷ ለዋጋ ሲሉ ያስተምራሉ፤ነቢያቷም ለገንዘብ ሲሉ ይናገራሉ።ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ተደግፈውም፣“እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን?ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይደርስብንም” ይላሉ።

12. ስለዚህ በእናንተ ምክንያት፣ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፣ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤የቤተ መቅደሱም ኰረብታ ዐረም የበቀለበት ጒብታ ይሆናል።

ሚክያስ 3