መዝሙር 99:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ከደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው፤እነርሱም ሥርዐቱንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ።

8. እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤አንተ መለስህላቸው፤ጥፋታቸውን ብትበቀልም እንኳ፣አንተ ይቅር የምትላቸው አምላክ ነህ።

9. አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤በቅዱስ ተራራውም ላይ ስገዱ፤አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።

መዝሙር 99