1. ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፤ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም፣ማዳንን አድርገውለታል።
2. እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።
3. ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ታማኝነቱንም አሰበ፤የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣የአምላካችንን ማዳን አዩ።
4. ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤
5. ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤
6. በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።
7. ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።
8. ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፤ተራሮችም በአንድነት ይዘምሩ፤