መዝሙር 97:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እግዚአብሔርን የምትወዱ ክፋትን ጥሉ፤እርሱ የታማኞቹን ነፍስ ይጠብቃልና፤ከዐመፀኞችም እጅ ይታደጋቸዋል።

11. ብርሃን ለጻድቃን፣ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።

12. እናንተ ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ።

መዝሙር 97