መዝሙር 91:2-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።

3. እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና።

4. በላባዎቹ ይጋርድሃል፤በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።

5. የሌሊትን አስደንጋጭነት፣በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤

6. በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም።

7. በአጠገብህ ሺህ፣ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃል፤ወደ አንተ ግን አይቀርብም።

8. በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ።

9. እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና።

10. ክፉ ነገር አያገኝህም፤መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤

11. በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋልና።

12. እግርህ ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣በእጆቻቸው ወደ ላይ ያነሡሃል።

13. በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

14. “ወዶኛልና እታደገዋለሁ፤ስሜን አውቆአልና እከልለዋለሁ።

መዝሙር 91