መዝሙር 90:12-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል?ለአገልጋዮችህም ራራላቸው።

14. በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን።

15. መከራ ባሳየኸን ዘመን መጠን፣ክፉም ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሰኘን።

16. ሥራህ ለአገልጋዮችህ፣ክብርህም ለልጆቻቸው ይገለጥ።

17. የጌታ የአምላካችን ሞገስ በላያችን ይሁን፤የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን፤አዎን፣ ፍሬያማ አድርግልን።

መዝሙር 90