መዝሙር 74:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የሌዋታንን ራሶች አደቀቅህ፤ለምድረ በዳ ፍጥረታትም ምግብ አድርገህ የሰጠሃቸው፣

15. ምንጮችንና ፈሳሾችን ያፈለቅህ አንተ ነህ፤ሳያቋርጡ የሚፈሱትንም ወንዞች አደረቅህ።

16. ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው፤ጨረቃንና ፀሓይን አንተ አጸናሃቸው።

17. የምድርን ዳርቻ ሁሉ የወሰንህ አንተ ነህ፤በጋውንም ክረምቱንም አንተ ሠራህ።

18. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላት እንዴት እንደሚያሾፍ፣ከንቱ ሕዝብም ስምህን እንዴት እንዳቃለለ አስብ።

መዝሙር 74