መዝሙር 63:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።

6. በመኝታዬ አስብሃለሁ፤ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።

7. አንተ ረዳቴ ነህና፣በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።

8. ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ብላለች፤ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች።

መዝሙር 63