መዝሙር 61:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. አምላክ ሆይ፤ ስእለቴን ሰምተሃልና፤ስምህን የሚፈሩትንም ሰዎች ርስት ለእኔ ሰጠህ።

6. የንጉሡን ዕድሜ አርዝምለት፤ዘመኑንም እስከ ብዙ ትውልድ ጨምርለት፤

7. በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ይንገሥ፤ይጠብቁት ዘንድ ምሕረትህንና ታማኝነትህን አዘጋጅለት።

8. ስለዚህ ለስምህ ዘወትር ውዳሴ አቀርባለሁ፤ስእለቴንም በየጊዜው እፈጽማለሁ።

መዝሙር 61