1. ቂል በልቡ፣“እግዚአብሔር የለም” ይላል።ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤በጎ ነገርን የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም።
2. በማስተዋል የሚመላለስ፣እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት፣እግዚአብሔር ከሰማይ፣ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።
3. ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤በአንድነትም ተበላሹ፤አንድ እንኳ፣በጎ የሚያደርግ የለም።
4. ሰው እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉት፣እግዚአብሔርንም ጠርተው የማያውቁት፣እነዚያ ክፉ አድራጊዎች ከቶ አይማሩምን?