መዝሙር 51:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ መጠን፣ምሕረት አድርግልኝ፤እንደ ርኅራኄህም ብዛት፣መተላለፌን ደምስስ።

2. በደሌን ፈጽሞ እጠብልኝ፤ከኀጢአቴም አንጻኝ።

3. እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፤ኀጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው።

4. በውሳኔህ ትክክል፣በምትሰጠው ፍርድም ንጹሕ ትሆን ዘንድ፣አንተን፣ በእርግጥ አንተን ብቻ በደልሁ፤በፊትህም ክፉ ነገር አደረግሁ።

መዝሙር 51