መዝሙር 44:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. አንተ ግን በጠላቶቻችን ላይ ድልን ትሰጠናለህ፤ባላንጣዎቻችንንም ታሳፍራለህ።

8. ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን፤ስምህንም ለዘላለም እንወድሳለን። ሴላ

9. አሁን ግን እነሆ ትተኸናል፤ አሳፍረኸናልም፤ከሰራዊታችንም ጋር አትወጣም።

10. ከጠላት ፊት እንድናፈገፍግ አደረግኸን፤ባላንጣዎቻችንም ዘረፉን።

11. እንደሚታረዱ በጎች አደረግኸን፤በሕዝቦችም መካከል በተንኸን።

መዝሙር 44