መዝሙር 44:21-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. እግዚአብሔር ይህን ማወቅ ይሳነዋልን?እርሱ ልብ የሰወረውን የሚረዳ ነውና።

22. ይሁን እንጂ ቀኑን ሙሉ ስለ አንተ ሞትን እንጋፈጣለን፤እንደሚታረዱ በጎችም ተቈጥረናል።

23. ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ?ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።

24. ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?መከራችንንና መጠቃታችንን ለምን ትረሳለህ?

25. ነፍሳችን ዐፈር ውስጥ ሰጥማለች፤ሆዳችንም ከምድር ጋር ተጣብቆአል።

26. ተነሥና እርዳን!ስለ ምሕረትህ ስትል ተቤዠን።

መዝሙር 44