መዝሙር 44:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ልባችን ወደ ኋላ አላለም፤እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም።

19. አንተ ግን ተኵላዎች በሚውሉበት ቦታ ሰባብረህ ጣልኸን፤በሞት ጥላም ሸፈንኸን።

20. የአምላካችንን ስም ረስተን፣እጃችንንም ወደ ባዕድ አምላክ ዘርግተን ቢሆን ኖሮ፣

21. እግዚአብሔር ይህን ማወቅ ይሳነዋልን?እርሱ ልብ የሰወረውን የሚረዳ ነውና።

22. ይሁን እንጂ ቀኑን ሙሉ ስለ አንተ ሞትን እንጋፈጣለን፤እንደሚታረዱ በጎችም ተቈጥረናል።

መዝሙር 44