መዝሙር 44:11-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እንደሚታረዱ በጎች አደረግኸን፤በሕዝቦችም መካከል በተንኸን።

12. ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው፤ከሽያጩም ያገኘኸው ትርፍ የለም።

13. ለጎረቤቶቻችን ስድብ፣በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።

14. በሕዝቦች ዘንድ መተረቻ፣በሰዎች መካከል በንቀት ራስ መነቅነቂያ አደረግኸን።

15. ውርደቴ ቀኑን ሙሉ በፊቴ ነው፤ፊቴም ዕፍረትን ተከናንቦአል።

16. ይህም ከሚዘልፍና ከሚያላግጥ ሰው ድምፅ የተነሣ፣ከጠላትና ከተበቃይ ሁኔታ የተነሣ ነው።

17. አንተን ሳንረሳ፣ለኪዳንህም ታማኝነታችንን ሳናጓድል፣ይህ ሁሉ ደረሰብን።

18. ልባችን ወደ ኋላ አላለም፤እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም።

19. አንተ ግን ተኵላዎች በሚውሉበት ቦታ ሰባብረህ ጣልኸን፤በሞት ጥላም ሸፈንኸን።

መዝሙር 44