መዝሙር 4:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ። ሴላ

5. የጽድቅን መሥዋዕት አቅርቡ፤ በእግዚአብሔርም ታመኑ።

6. ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል? ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ።

7. ስንዴና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ባመረቱ ጊዜ ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ፣አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል።

8. በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።

መዝሙር 4