መዝሙር 17:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ልቤን መረመርኸው፣ በሌሊት ጠጋብለህ ፈተንኸኝ፤ፈተሽኸኝ አንዳች አላገኘህብኝም፤አንደበቴም ዕላፊ አልሄደም።

4. ከሰዎች ተግባር፣በከንፈርህ ቃል፣ከዐመፀኞች መንገድ፣ራሴን ጠብቄአለሁ።

5. አረማመዴ በመንገድህ ጸንቶአል፤እግሮቼም አልተንሸራተቱም።

6. አምላክ ሆይ፤ ስለምትመልስልኝ አንተን እጣራለሁ፤ጆሮህን ወደ እኔ ጣል አድርገህ ጸሎቴን ስማ።

7. ከጠላቶቻቸው መተገኛ ያደረጉህን፣በቀኝ እጅህ የምትታደግ ሆይ፤ጽኑ ፍቅርህን ድንቅ አድርገህ ግለጥ።

8. እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤

9. ከሚያስጨንቁኝ ከክፉዎች፣ከሚከብቡኝ አደገኛ ባላንጣዎቼ ጋርደኝ።

መዝሙር 17