መዝሙር 14:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሞኝ በልቡ፣“እግዚአብሔር የለም” ይላል።ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤በጎ ነገር የሚሠራ አንድም የለም።

2. የሚያስተውል፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ መኖሩን ለማየት፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።

3. ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤በአንድ ላይም ብልሹ ሆነዋል፤አንድ እንኳ፣መልካም የሚያደርግ የለም።

መዝሙር 14