መዝሙር 139:13-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. አንተ ውስጣዊ ሰውነቴን ፈጥረሃልና፤በእናቴም ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ።

14. ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ሥራህ ድንቅ ነው፤ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች።

15. እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፣ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተደበቁም፤በምድር ጥልቀት ውስጥ በጥበብ በተሠራሁ ጊዜ፣

16. ዐይኖችህ ገና ያልተበጀውን አካሌን አዩ፤ለእኔ የተወሰኑልኝም ዘመናት፣ገና አንዳቸው ወደ መኖር ሳይመጡ፣በመጽሐፍ ተመዘገቡ።

17. አምላክ ሆይ፤ ለእኔ ያለህ ሐሳብ እንዴት ክቡር ነው!ቍጥሩስ ምንኛ ብዙ ነው!

18. ልቍጠራቸው ብል፣ከአሸዋ ይልቅ ይበዙ ነበር።ተኛሁም ነቃሁም፣ገና ከአንተው ጋር ነኝ።

19. አምላክ ሆይ፣ ክፉዎችን ብትገድላቸው ምናለበት!ደም የተጠማችሁ ሰዎች ሆይ፤ከእኔ ራቁ!

20. ስለ አንተ በክፋት ይናገራሉና፤ጠላቶችህም ስምህን በከንቱ ያነሣሉ።

21. እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚጠሉህን አልጠላምን?በአንተ ላይ የሚነሡትንስ አልጸየፍምን?

22. በፍጹም ጥላቻ ጠልቻቸዋለሁ፤ባላጋራዎቼም ሆነዋል።

23. እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤

24. የክፋት መንገድ በውስጤ ቢኖር እይ፤በዘላለምም መንገድ ምራኝ።

መዝሙር 139