መዝሙር 134:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንት በሌሊት ቆማችሁ በእግዚአብሔር ቤት የምታገለግሉ፣ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ።

2. በመቅደሱ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፤ እግዚአብሔርንም ባርኩ።

3. ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር፣ከጽዮን ይባርክህ።

መዝሙር 134