መዝሙር 116:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?

13. የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

14. በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።

15. የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።

16. እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፣ከእስራቴም ፈታኸኝ።

መዝሙር 116