መዝሙር 110:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰዳል፤አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።

3. ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ከንጋት ማሕፀን፣በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣የጐልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።

4. “እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት፤አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣ እግዚአብሔር ምሎአል፤እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።

5. ጌታ በቀኝህ ነው፤በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቃቸዋል።

6. በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤በየአገሩ ያሉትንም ራሶች ከስክሶ ሬሳ በሬሳ ያደርጋቸዋል።

7. መንገድ ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል፤ስለዚህ ራሱን ቀና ያደርጋል።

መዝሙር 110