መዝሙር 109:28-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. እነርሱ ይራገማሉ፤ አንተ ግን ትባርካለህ፤በሚነሡበት ጊዜ ይዋረዳሉ፤ባሪያህ ግን ሐሤት ያደርጋል።

29. የሚወነጅሉኝ ውርደትን ይከናነቡ፤ዕፍረትንም እንደ ሸማ ይልበሱ።

30. እግዚአብሔርን በአንደበቴ እጅግ አመሰግናለሁ፤በታላቅ ሕዝብም መካከል አወድሰዋለሁ።

31. በነፍሱ ላይ ከሚፈርዱት ያድነው ዘንድ፣እርሱ በችግረኛው ቀኝ በኩል ይቆማልና።

መዝሙር 109