መዝሙር 109:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የምስጋናዬ ምንጭ የሆንህ አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤

2. ክፉዎችና አታላዮች፣አፋቸውን ከፍተውብኛልና፤በውሸተኛ አንደበት ተናግረውብኛል።

3. በጥላቻ ቃል ከበውኛል፤ያለ ምክንያትም ጥቃት አድርሰውብኛል።

4. ስወዳቸው ይወነጅሉኛል፤እኔ ግን እጸልያለሁ።

5. በበጎ ፈንታ ክፋትን፣በወደድኋቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል።

መዝሙር 109