1. የምስጋናዬ ምንጭ የሆንህ አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤
2. ክፉዎችና አታላዮች፣አፋቸውን ከፍተውብኛልና፤በውሸተኛ አንደበት ተናግረውብኛል።
3. በጥላቻ ቃል ከበውኛል፤ያለ ምክንያትም ጥቃት አድርሰውብኛል።
4. ስወዳቸው ይወነጅሉኛል፤እኔ ግን እጸልያለሁ።
5. በበጎ ፈንታ ክፋትን፣በወደድኋቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል።
6. ክፉ ሰው በላዩ ሹም፤ከሳሽም በቀኙ ይቁም።
7. ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ ሆኖ ይገኝ፤ጸሎቱም ለፍርድ ትሁንበት።
8. ዕድሜው ይጠር፤ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው።
9. ልጆቹ ድኻ አደጎች ይሁኑ፤ሚስቱም መበለት ትሁን።
10. ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ፤ከፈረሰው ቤታቸውም ይሰደዱ።