መክብብ 8:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነገሮችን መግለጽ የሚችል፣እንደ ጠቢብ ያለ ሰው ማን ነው?ጥበብ የሰውን ፊት ታበራለች፤የከበደ ገጽታውንም ትለውጣለች።

2. በእግዚአብሔር ፊት መሐላ ስለፈጸምህ፣ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር እልሃለሁ።

3. ከንጉሥ ፊት ተጣድፈህ አትውጣ፤ የወደደውንም ማድረግ ስለሚችል ለጥፋት አትሰለፍ።

መክብብ 8