መክብብ 3:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤

2. ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤

3. ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤

መክብብ 3