እንደ ገና ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ አስተዋልሁም፤የተገፉትን ሰዎች እንባ ተመለከትሁ፤የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ኀይል በሚገፏቸው ሰዎች እጅ ነበረ፤የሚያጽናናቸውም አልነበረም።