መክብብ 2:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እኔም በልቤ፣ “መልካም የሆነውን ለማወቅ፣ በተድላ ደስታ እፈትንሃለሁ” አልሁ፤ ነገር ግን ያም ከንቱ ነበረ።

2. ደግሞም፣ “ሣቅ ሞኝነት ነው፤ ተድላ ደስታስ ምን ይጠቅማል?” አልሁ።

3. አሁንም አእምሮዬ በጥበብ እየመራኝ ራሴን በወይን ጠጅ ደስ ለማሰኘት፣ ሞኝነትንም ለመያዝ ሞከርሁ፤ ሰዎች በአጭር የሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ባለው ላይ ቢሠሩት ሊጠቅማቸው የሚችል ምን እንደሆነ ለማየት ፈለግሁ።

4. ታላላቅ ነገሮችን አከናወንሁ፤ ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፤ ወይንንም ተከልሁ፤

5. አትክልትን ተከልሁ፤ የመዝናኛ ስፍራዎችን አዘጋጀሁ፤ በእነዚህም ላይ ፍሬ የሚያፈሩ የዛፍ ዐይነቶችን ሁሉ ተከልሁባቸው፤

6. የሚለመልሙ ዛፎችን ለቦይ የሚሆኑ የውሃ ማጠራቀሚያዎችን ሠራሁ።

መክብብ 2