ሆሴዕ 7:13-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ወዮ ለእነርሱ፤ከእኔ ርቀው ሄደዋልና!ጥፋት ይምጣባቸው!በእኔ ላይ ዐምፀዋልና።ልታደጋቸው ፈለግሁ፤እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።

14. ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፤ነገር ግን በዐልጋቸው ላይ ሆነው ያለቅሳሉ።ስለ እህልና ስለ አዲስ የወይን ጠጅይሰበሰባሉ፤ነገር ግን ከእኔ ዘወር ብለዋል።

15. እኔ አሠለጠንኋቸው፤ አጠነከርኋቸውም፤እነርሱ ግን አደሙብኝ።

16. ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ዒላማውን እንደሳተ ቀስት ናቸው፤መሪዎቻቸው ስለ ክፉ ቃላቸው፣በሰይፍ ይወድቃሉ፤በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር፣መዘባበቻ ይሆናሉ።

ሆሴዕ 7