ሆሴዕ 6:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. እንደ አዳም ቃል ኪዳንን ተላለፉ፤በዚያም ለእኔ ታማኝ አልነበሩም።

8. ገለዓድ በደም የተበከለች፣የክፉዎች ሰዎች ከተማ ናት።

9. ወንበዴዎች ሰውን ለማጥቃት እንደሚያደቡ፣ካህናትም በቡድን እንዲሁ ያደርጋሉ፤በሴኬም መንገድ ላይ ሰዎችን ይገድላሉ፤አሳፋሪም ወንጀል ይፈጽማሉ።

10. በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ፤በዚያ ኤፍሬም ዘማዊ ሆነ፤እስራኤልም ረከሰ።

11. “ይሁዳ ሆይ፤ ለአንተም፣መከር ተመድቦብሃል።ሕዝቤን ከምርኮ አገር በመለስሁ ጊዜ፣

ሆሴዕ 6